የምክር ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች የምክር ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች

ራዕይ

በሕገ መንግሥቱ ተረጋገጠው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ና ሕዝቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ና ዲሞክራሲያዊ አንድነት ዘብ የቆመ ምክር ቤት ሆኖ ማየት፣

ተልዕኮ

ሕገ-መንግስቱን በመተርጎም፣ የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ውሳኔ በመስጠት፣ ፍትሃዊ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በመወሰን፣ ሊፈጠሩ ለሚችሉ ግጭቶችንና አለመግባባቶች ውሳኔ በመስጠት፣ በየሰመረ የመንግሥታት ግንኙነት በማዳበር፣ በሕ/ተ/ም/ቤት ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሃ ብሔር ጉዳዮችን በመለየት፣ ንቃተ ሕገ-መንግሥት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ግንኙነትን በማጠናከር ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ማድረግ፣

ዕሴቶች

ሀ/ ሕገ መንግሥታዊነት፣

ለ/ ዴሞክራሲያዊነት፣

ሐ/ ፍትሃዊነት እና/ወይም እኩልነት፣

መ/ ተዓማኒነት፣

ሠ/ አሳታፊነት፣

ረ/ አጋርነት፣

ሰ/ ግልጸኝነት፣

ሸ/ ወቅታዊ ምላሽ፣

አድራሻ አድራሻ

ስልክ ቁ: +251-111-242-301/3

ስልክ ቁ:  +251-111-242-309

ስልክ ቁ:  +251-111-223-322


ፋክስ+251-111-242-304/8

ፋክስ:  +251-111-241-208

የፖ.. ቁጥር:  20212/1000

አዲ አበባ፣ ኢትዮዽያ

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት፣ ተግባር እና ኃላፊነት የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት፣ ተግባር እና ኃላፊነት

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢፌዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 61 የተመሠረተ፣ በአገራችን ክልሎች የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና የሚረጋገጥበት የፌዴራል ምክር ቤት ነው፡፡ በዚህ ምክር ቤት እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ ቢያንስ በአንድ ተወካይ የሚወከል ሲሆን ለያንዳንዱ አንድ ሚሊየን ሕዝብ ተጨማሪ አንድ ወኪል ይኖረዋል፡፡ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ምክር ቤቶች አማካይነት ነው፡፡ ምርጫው በቀጥታ አሊያም ደግሞ በተዘዋዋሪ ሊካሄድ ይችላል፤ ይህም ማለት የክልል ምክር ቤቶች አባላቱን በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሚደረግ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲመረጡ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በ5ኛው የምክር ቤት ዘመን፣ ምክር ቤቱ በአጠቃላይ 153 አባላት የነበሩት ሲሆን 76 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችም ተወክለዋል፡፡

Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተመሠረተው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በጸደቀበት 1987 ዓ.ም. ነው፡፡ ምክር ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ አምስተኛ የምክር ቤት ዘመን በማገባደድ ላይ ነው፡፡ በምክር ቤቱ ባለፉት አምስት የምክር ቤት ዘመን የሥራ ዓመታት የነበረው የአባላት ውክልና በየጊዜው እያደገ እና እየሰፋ መጥቷል፡፡ በመጀመሪያው የምክር ቤት ዘመን (ከ1987 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም.) 108 አባላት የነበሩት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1993 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም.)የአባላቱ ቁጥር ወደ 112 ያደገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴቶች ብዛት 8 ሆኖ ነበር፡፡ በሦስተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1998 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም.)የምክር ቤቱ አባላት ብዛት 121 ሲደርስየሴቶች ቁጥርም 22 ደርሷል፡፡ በአራተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ2003 ዓ.ም.እስከ 2007 ዓ.ም.) የምክር ቤቱ አባላት 135 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴት አባላት ቁጥር ወደ 23 ከፍ ብሏል፡፡ በአምስተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ2008 ዓ.ም.እስከ 2012 ዓ.ም.) የምክር ቤቱ አባላት 153 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴት አባላት ቁጥር ወደ 50 ከፍ ብሏል፡፡ የምክር ቤቱን የብሔረሰብ ውክልናም ስናይ እድገት አሳይቷል፡፡ ይህም እውቅና እያገኙ የመጡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቁጥር መጨመሩን ያሳያል፡፡  በመሆኑም  በ5ቱ የምክር ቤት ዘመኖች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቁጥር እንደየ ቅደም ተከተላቸው 56፣ 58፣ 67፣ 75 እና 76 ደርሷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች / Speakers of the House of Federation

Name

Entered Office

Left Office

Almaz Meko

አልዝ መኮ

1995

August 2001

Mulatu Teshome

ሙላቱ  ተሾመ

10 October 2002

10 October 2005

Degefe Bula

ደግፌ ቡላ

10 October 2005

2010

Kasa Teklebirhan

ካሳ ተክለብርሀን

2010

October 2015

Yalew Abate

ያለው አባተ

October 2015

6 May 2018

Keria Ibrahim

ኬሪያ ኢብራሂም

6 May 2018

 


አሰተያየት እና ጥቆማ አሰተያየት እና ጥቆማ

እባክዎ አሰተያየት እና ጥቆማዎትን በዚህ ቅጽ ይላኩልን. ከአንድ በላይ አባሪ ካሎት ወደ አንድ ቀይረው (ዚፕ አድርገው) ይላኩ፡፡

This field is mandatory.
This field is mandatory.
Text to Identify Refresh CAPTCHA Refresh CAPTCHA