የምክር ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች የምክር ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች

ራዕይ

በሕገ መንግሥቱ ተረጋገጠው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ና ሕዝቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ና ዲሞክራሲያዊ አንድነት ዘብ የቆመ ምክር ቤት ሆኖ ማየት፣

ተልዕኮ

ሕገ-መንግስቱን በመተርጎም፣ የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ውሳኔ በመስጠት፣ ፍትሃዊ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በመወሰን፣ ሊፈጠሩ ለሚችሉ ግጭቶችንና አለመግባባቶች ውሳኔ በመስጠት፣ በየሰመረ የመንግሥታት ግንኙነት በማዳበር፣ በሕ/ተ/ም/ቤት ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሃ ብሔር ጉዳዮችን በመለየት፣ ንቃተ ሕገ-መንግሥት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ግንኙነትን በማጠናከር ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ማድረግ፣

ዕሴቶች

ሀ/ ሕገ መንግሥታዊነት፣

ለ/ ዴሞክራሲያዊነት፣

ሐ/ ፍትሃዊነት እና/ወይም እኩልነት፣

መ/ ተዓማኒነት፣

ሠ/ አሳታፊነት፣

ረ/ አጋርነት፣

ሰ/ ግልጸኝነት፣

ሸ/ ወቅታዊ ምላሽ፣

አድራሻ አድራሻ

ስልክ ቁ: +251-111-242-301/3

ስልክ ቁ:  +251-111-242-309

ስልክ ቁ:  +251-111-223-322


ፋክስ+251-111-242-304/8

ፋክስ:  +251-111-241-208

የፖ.. ቁጥር:  20212/1000

አዲ አበባ፣ ኢትዮዽያ

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት፣ ተግባር እና ኃላፊነት የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት፣ ተግባር እና ኃላፊነት

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት ተግባርና ኃላፊነት

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢፌዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 61 የተመሠረተ፣ በአገራችን ክልሎች የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና የሚረጋገጥበት የፌዴራል ምክር ቤት ነው፡፡ በዚህ ምክር ቤት እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ ቢያንስ በአንድ ተወካይ የሚወከል ሲሆን ለያንዳንዱ አንድ ሚሊየን ሕዝብ ተጨማሪ አንድ ወኪል ይኖረዋል፡፡ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ምክር ቤቶች አማካይነት ነው፡፡ ምርጫው በቀጥታ አሊያም ደግሞ በተዘዋዋሪ ሊካሄድ ይችላል፤ ይህም ማለት የክልል ምክር ቤቶች አባላቱን በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሚደረግ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲመረጡ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በ5ኛው የምክር ቤት ዘመን፣ ምክር ቤቱ በአጠቃላይ 153 አባላት የነበሩት ሲሆን 76 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችም ተወክለዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 እና በአዋጅ ቁጥር 251/93 መሠረት በርካታ አገራዊ አንደምታ ያላቸውና ልዩ የሆኑ ወሳኝ ሥልጣንና ተግባራት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 ላይ ተሠጥተውታል፡፡ ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ሥልጣን አለው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን ያደራጃል፡፡ ሕገ መንግሥቱን ከመተርጎም አንጻር ምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት የሚያቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሠጣል፤ አጣሪ ጉባኤው ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት በሠጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሚቀርቡ ይግባኞችንም በመመርመር ይወስናል፡፡

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብትን በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የመወሰን ሥልጣንም የምክር ቤቱ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ማንነቴ አልታወቀልኝም፣ የራስ በራስ የማስተዳደር መብቴ ተሸራርፏል፣ ቋንቋዬን፣ ባህሌንና ታሪኬን የማሳድግበት ሁኔታ አልተመቻቸልኝም፣ በአጠቃላይ በፌዴራል ሕገ መንግሥት የተደነገገው መብቴ አልተከበረም ወይም በማንኛውም ሌላ ምክንያት አድልዎ ተፈጽሞብኛል በማለት ለሚያቀርበው ጥያቄ ውሳኔ ይሠጣል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብሔር ብሔረሰቦች ለሚያቀርቡት ክልል የመሆንና የመገንጠል ጥያቄዎች በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምላሽ ይሠጣል፡፡

ሌላው የምክር ቤቱ ሥልጣን የሕዝቦችን እኩልነትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ማድረግ ነው፡፡ ይህንንም ለመተግበር አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመመካከር የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ባህል እና ንቃተ ሕገ መንግሥት ለማዳበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶች በየወቅቱና በየአካባቢው ያከናውናል፡፡ በየደረጃው ያሉት የትምህርት ተቋማት በሕዝቦች መካከል እኩልነትና አንድነትን የሚያጠናክሩ የትምህርት ዓይነቶች በሥርዓተ ትምህርታቸው ማካተታቸውን ይከታተላል፤ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንም ለጉዳዩ በቂ ሽፋንና አምድ መመደባቸውን ይከታተላል፤ ለሕዝቦች እኩልነትና አንድነት መጠናከር እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ አመለካከቶችና አዝማሚያዎች በማጥናትና በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ቀይሶ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያስፈጽሟቸው ያደርጋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ በክልሎች መካከል ያለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲጠናከርና በሕዝቦች መካከል እኩልነትና አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብርም ክልሎች በየዓመቱ የሚመደብላቸውን በጀት በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን አቅም እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠንና በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ይወስዳል፤ የፌዴራል የልማት አውታሮች ሥርጭት ለኢንቨስትመንት ትርጉም ያለውና ፍትሃዊ መሆናቸውን ይከታተላል፤ በፌዴራል ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የመንግሥት አወቃቀርና የሥልጣን ክፍፍል መሠረት በማድረግ ክልሎች የሚረዱበትንና በጋራ ለጋራ ጥቅም የሚሰሩበትን መድረኮች እና ሁኔታዎች ያመቻቻል፣ እየተጠናከሩ እንዲሄዱም ድጋፍ ይሠጣል፤ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል የመቻቻልና ለጋራ ዓላማ የመሥራት ባህል እንዲዳብር እንዲሁም አንድነታቸው እንዲጠናከር የሚያስችሉ እርምጃዎችን ይወስዳል፤ በእድገት ወደኋላ የቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በሰው ኃይል ሥልጠናና በሌሎች መስኮች ልዩ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡

በክልሎች መካከል ወሰንን በሚመለከትም ይሁን በሌሎች ምክንያቶች የሚነሱ እንዲሁም በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶች በስምምነት ሊፈቱ ካልቻሉ የመጨረሻ መፍትሔ የሚያገኙትም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ከዚህ አንፃር የሚነሱ አለመግባባቶችን ለማስወገድ የሚረዱ ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ የግጭት መከላከያና ማስወገጃ ስልቶችን በማጥናት የአሠራር ሥርዓትና ስልት ይዘረጋል፡፡ ተቋማዊ ይዘትና አደረጃጀት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

የክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለት መካከል የሚከፋፈሉበትን፣ እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመሮች መወሰንም ሌላው የምክር ቤቱ ሥልጣን ነው፡፡ በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ተጨባጭነትና ተቀባይነት ያለው በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ፍትሃዊና ውጤታማ የገቢ ማከፋፈያ ቀመሮችን የማዘጋጀትና የገቢ ክፍፍሉ ክልሎችን ከድጎማ በማላቀቅና የክልሎችን የተመጣጠነ ዕድገት በማምጣት ረገድ ያለውን አንደምታ በማጥናት ማስተካከያዎችን የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

ከላይ ከተገለጹት ሥልጣንና ተግባራት በተጨማሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር አስፈላጊ የሆኑ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን ይለያል፤ ማንኛውም ክልል ሕገ መንግስቱን በመጣስ ሕገ መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል፤ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች አከላለልን አስመልክቶ የሚያቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብ የሕዝቦችን ሚዛናዊና ተመጣጣኝ ውክልና የማግኘት መብት የሚያስጠብቅ መሆኑን በመመርመር ያጸድቃል፤ ለፌዴራል ወይም ለክልል መንግስታት ተለይተው ባልተሰጡ ታክስና ግብር የመጣል ሥልጣን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በጋራ ይወስናል፤ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በሚደረግ የጋራ ስብሰባ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ይመርጣል፤ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 105 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 በተገለጸው መሠረት ሕገመንግስቱን በማሻሻል ሂደት ይሳተፋል፤ እንዲሁም በስልጣኑ ሥር በሚካተቱ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች ጋር በመተባበር ሥልጠናና ግንዛቤ ይሠጣል፡፡

ምክር ቤቱ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባርና ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 እና በአዋጅ እና የምክር ቤቱን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 39 እና 40 በተገለጸው መሠረት፣ የራሱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ በመምረጥና ሁለት ቋሚ ኮሚቴዎችን በማደራጀት ሥራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር ምክር ቤቱ የተሠጠውን ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል የራሱን ጽሕፈት ቤት በአዋጅ ቁጥር 556/2006 መሠረት አቋቁሟል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በምክር ቤቱ የሚሾም ኃላፊ ያለው ሲሆን፣ በአፈ ጉባኤ የሚመደቡ ዳይሬክተሮችና በሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የሚመደቡ ሠራተኞች አሉት፡፡

አስተባባሪ ኮሚቴ

  • አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ፣
  • የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ጸሐፊዎች፣
  • ጽ/ቤት ኃላፊ፣

ሦስት ቋሚኮሚቴዎች

  • የበጀት ድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳዮች፣
  • የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች፣
  • የዴሞክራሲያዊአንድነት፣ የግጭት አፈታትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ጉዳዮች፣

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተመሠረተው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በጸደቀበት 1987 ዓ.ም. ነው፡፡ ምክር ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ አምስተኛ የምክር ቤት ዘመን በማገባደድ ላይ ነው፡፡ በምክር ቤቱ ባለፉት አምስት የምክር ቤት ዘመን የሥራ ዓመታት የነበረው የአባላት ውክልና በየጊዜው እያደገ እና እየሰፋ መጥቷል፡፡ በመጀመሪያው የምክር ቤት ዘመን (ከ1987 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም.) 108 አባላት የነበሩት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1993 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም.)የአባላቱ ቁጥር ወደ 112 ያደገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴቶች ብዛት 8 ሆኖ ነበር፡፡ በሦስተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1998 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም.)የምክር ቤቱ አባላት ብዛት 121 ሲደርስየሴቶች ቁጥርም 22 ደርሷል፡፡ በአራተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ2003 ዓ.ም.እስከ 2007 ዓ.ም.) የምክር ቤቱ አባላት 135 ሲሆን...

አሰተያየት እና ጥቆማ አሰተያየት እና ጥቆማ

እባክዎ አሰተያየት እና ጥቆማዎትን በዚህ ቅጽ ይላኩልን. ከአንድ በላይ አባሪ ካሎት ወደ አንድ ቀይረው (ዚፕ አድርገው) ይላኩ፡፡

This field is mandatory.
This field is mandatory.
Text to Identify Refresh CAPTCHA Refresh CAPTCHA