ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች

ራዕይ

2023 የሕገመንግስት የበላይነትና ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ሕብረብሔራዊ አንድነትና ዘላቂ ሰላም የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መገንባት፡

ተልዕኮ

ሕገ መንግሥቱን በመተርጎም፣ በመፈቃቀድና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ የሕዝቦች አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር በማድረግ፣ በክልሎች መካከል ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ግንኙነቶችን በማዳበር፣ ፍትሀዊና ውጤታማ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በማዘጋጀትና በመወሰን፣ ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በማጥናትና በመለየት፣ እንዲሁም ዜጎች ሕገ መንግሥቱን ጠንቅቀው አውቀው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት በቁርጠኝነት መሥራት፣

ዕሴቶች

  • ትክክለኛና አድልዎ የሌለበት ውሳኔ መስጠት፣
  • በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፆታና በፖለቲካ አመለካከት ወዘተ... ልዩነት ሳይደረግ ሁሉንም በእኩልነት ማገልገል፣
  •  የሚመለከታቸውን ሁሉ በማሳተፍ የተለያዩ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነጻ እንዲንሸራሸሩ ማድረግ፣
  •  የምክር ቤቱን ባለድርሻዎች በቅንነት ማገልገል፣
  • ባለድርሻዎችን ሊያሳትፍ በሚያስችል ግልጽ አሰራር ላይ ተመስርቶ ማከናወንና የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔዎች በግልፅ ማድረግ፣
  • ለሕገ መንግሥቱ፣ ለሕዝቡ፣ ለሕሊናቸው፣ እንዲሁም /ቤቱ ለሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ታማኝና ተገዢ መሆን፣
  • ማናቸውንም አመለካከቶችና ልዩነቶች በመቻቻልና በመከባበር መንፈስ ማስተናገድ፣
  • አቤቱታዎችን በሕገ መንግሥቱና በአዋጅ በተቀመጡ

የጽህፈት ቤቱ - ዓላማ, ስልጣንና, ተግባር የጽህፈት ቤቱ - ዓላማ, ስልጣንና, ተግባር

Secretariat - Powers & Duties

ከ1993 ዓ.ም በፊት ምክር ቤት የራሱ ጽሕፈት ቤት አልነበረውም፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው በ1993 ዓ.ም. ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ የሕግ ሰውነት አልነበረውም፡፡ ሕግ ሰውነት ያገኘው በአዋጅ ቁጥር 556/2000 ነው፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለአፈ ጉባኤው ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች አሉት፡

1  ለምክር ቤቱና ምክር ቤቱ ለሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎች፣ ለአፈ-ጉባዔዎች፣ ለምክር ቤቱ አባላት አጠቃላይ አስተዳደራዊ፣ የጽሕፈት፣ የመስተንግዶና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል

2 በአፈ-ጉባዔው ወይም በምክትል አፈ-ጉባዔው ውሳኔ መሠረት በወቅቱ ለአባላት የስብሰባ ጥሪ ያስተላልፋል፣ አጀንዳዎችንና ተፈላጊ ሰነዶችንም ያሰራጫል፤

3  የምክር ቤቱና የአፈ-ጉባዔዎች እንግዶች አስፈላጊውን የመስተንግዶ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

4  የምክር ቤቱንና የጽሕፈት ቤቱን፡-

ሀ/  ቃለ-ጉባኤዎች፣ ውሳኔዎች፣ አቋሞች፣ ሰነዶችና መዛግብቶች፣ እና

ለ/  አስፈላጊ የሆኑ መጽሐፍት፣ ጥናታዊ ጽሑፎችና መረጃዎች በአግባቡ ተሰብስበው፣ ተመዝግበውና ተደራጅተው አገልግሎት እንዲሰጡና እንዲጠበቁ ያደርጋል፤

5 የምክር ቤቱንና የጽሕፈት ቤቱን አቋም አሰራርና ተልዕኮ የሚመለከቱ ጉዳዮችን የያዙ መጽሔቶች፣ ጋዜጦችና በራሪ ጽሑፎች አዘጋጅቶ እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ያደርጋል፤

6 በምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባር፣ አሠራር፣ አደረጃጀትና አግባብነት ባላቸው ሕጎች ዙሪያ ጥናትና ምርምር እንዲያደርግ ሲታዘዝ ጥናት ያካሂዳል፣ ውጤቱንም ከሙያዊ አስተያየት ጋር ያቀርባል፤

7  የክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡና የተሰበሰቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ቀመር የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት አዘጋጅቶ ለኮሚቴው ያቀርባል፤

8  የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጉዳዮችን በማጣራት በሚሰጠው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ምክር ቤቱ ተጨማሪ የባለሙያ አስተያየት ሲጠይቅ ወይም የሕገመንግሥት ትርጉም አያስፈልግም በማለት በሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሲቀርብ ቋሚ ኮሚቴው በሚያዘው መሠረት ጥናት አድርጎ ሙያዊ አስተያየት ያቀርባል፤

9  ሕዝቡ ስለ ሕገ መንግሥቱና ስለምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባራት እንዲያውቅ ከሚመ ለከተው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመሆን በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እንዲሰራ ያደርጋል፤

10  አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያግዙና ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን ቋሚ ኮሚቴው በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት ያጠናል፣ ይለያል፣ ለኮሚቴ ያቀርባል፤

11 ምክር ቤቱ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የማንነት ጥናት ያካሂዳል፣ የጥናቱንም ውጤት ለሚመለከተው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ያቀርባል፤

12 በክልሎችና በሕዝቦች መካከል ያሉ አለመግባባቶች እንዲጠኑ ሲታዘዝ የዳሰሳ፣ የትንተናና የመከላከያ ስትራቴጂ በማጥናት የጥናቱን ውጤት ለኮሚቴው ያቀርባል፤

13 የምክር ቤቱ የአገር ውስጥና የውጪ ግንኙነት የተሳካና የተቃና እንዲሆን አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤

14 በክልሎች መካከል በተከሰተ አለመግባ ባት፣ በብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የመብት ጥያቄ መነሻነት ለምክር ቤቱ የቀረቡ አቤቱታዎች ሲመሩለት እና በሚሰጠው መመሪያ መሠረት መርምሮና አጣርቶ ለሚመለከተው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አስተያየት ያቀርባል፣

15 ምክር ቤቱ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አፈፃፀምና ያስገኙት ውጤት በተመለከተ በአፈ-ጉባዔው ሲታዘዝ ክትትልና ግምገማ በማድረግ ሙያዊ አስተያየት ያቀርባል፤

16 የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፣

17 በምክር ቤቱና በአፈ-ጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡


አሰተያየት እና ጥቆማ አሰተያየት እና ጥቆማ

እባክዎ አሰተያየት እና ጥቆማዎትን በዚህ ቅጽ ይላኩልን. ከአንድ በላይ አባሪ ካሎት ወደ አንድ ቀይረው (ዚፕ አድርገው) ይላኩ፡፡

This field is mandatory.
This field is mandatory.
Text to Identify Refresh CAPTCHA Refresh CAPTCHA