እንኳን ለ124ኛው የአድዋ ድል ክበረ በዓል አደረሰን!

ኢትዮጵያ የጥቁር አፍሪካዊያን፣ የነፃነት ፋና ወጊ ናት። ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገርና ለአፍሪካዊያን የነፃነት ተምሳሌት ናት። ሁሉም ዓለም ጥቁር ሕዝቦች ነፃ እንዲወጡ ከፍተኛ ሚና የተጫወተች በመሆኗም ሁሌም በታሪክ ስትወሳ ትኖራለች። ለዓለም መድረክ ስሟ እንዲገን ከአስቻሏት አንዱና ዋነኛው ደግሞ ታላቁ የአድዋ እንደሆነ ይጠቀሳል። ድሉ ለእኛ ለኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የነፃነታችን ብቻ ሳይሆን የአንድነታችን፣ የብዝኃነታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ መሆኑን ያሳየንበት ጭምር ነው።
የዘንድሮው 124ኛው በዓል “አድዋ የሰውነት ማህተም፣ የአንድነታችን ድር እና ማግ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ይታወቃል። ለሀገር ነፃነት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉት አያቶቻችን ጀግንነትና ቆራጥነት እየተማርንና የአድዋን የመደመር እሳቤ ይዘን በዓሉን በየዓመቱ በማክበርና በመዘከር በሀገራችን የተጀመሩትን ሁለንተናዊ የልማት እና ዕድገት መስመር በማስቀጠል፤ በአገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን፣ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን መሥራት ይጠበቅብናል።

የካቲት20/06/2012ዓ.ም
መልካም የአድዋ ድል ክበረ በዓል!!