ሚዲያ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓትና ሀገርን የማዳን ጥያቄ በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ውይይት ተካሄደ፤

ነሐሴ 18 / 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ፦ /በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የውስጥና የውጭ ሃይሎች ጥምረት ፈጥረው ግልጽ የውክልና ጦርነት ከፈተው እልህ እስጨራሽ የሕልውና ትግል ሀገራችን እያደረገች ትገኛለች፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ ሀገርን ከብተና፣ ሕዝብን ደግሞ ከአደጋ ለመከላከልና ለመታደግ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመተባበር የሕልውና ዘመቻን በቁርጠኝነት እያከናወኑ እንደሚገኝ የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ም/አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ዕፀገነት መንግስቱ ገለጻዋል ፡፡ ወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደ ጥንቱ እንደ ታላቁ አድዋ የውስጥና የውጭ አፍራሽ ሃይሎች ሀገራችንን ለመበታተን አሴረው የከፈቱብን ን ጦርነት በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት በመመከት ላይ የምንገኘበት ጊዜ ሲሆን የትግራይ ሕዝብም በስምህ ከሚነግደው ከሃዲና አሽባሪ ሕወሃት ቡድን ራስህን በመለየት ከሌሎች ወንድምና እህት ሕዝቦች ጋር በመሆን ለሀገር አንድነትና ለሠላምና ለልማት እንድት ስልፉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል ። ይህንን በተመለከተም የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣የጽ/ቤቱ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች በሕልውናው ዘመቻ በግንባር ላይ የሚፋለሙና ለሚዋደቁ ለጀግና መከላከያ ሰራዊታችን ‹‹ደሜ ለመከላከያ ሰራዊታችን›› የሚል መሪ ሃሳብ በማንገብ የደምና የገንዘብ ልገሳ በማድረግ ድጋፋችውን መግለጻቸውን አውሰተው አሁንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሕብረ ብሄራዊ አንድነት በይበልጥ እንዲጠናከር፣ እኩል ተሳትፎንና የጋራ ሃብቱን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በጠንካራ ክንድ የተገነባች ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ለቀጠዩ ትውልድ ለማሰተላለፍ የበኩሉን ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮ እየተወጣ ነው ብለዋል፡ እንዲሁም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ም/አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ዕፅገነት መንግስቱ 16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከትም ከሌሎች ጊዜያት በተለየ የሕዝቦችን እኩልነት፣አንድነትና ትስስርን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበርና እቅዱ ከዚህ አኳያ ተቃኝቶ እየተዘጋጀ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በዓሉ ከዚህ ዓላማ አንፃር ያመጣው ለውጥና ውጤት እየተገመገመና እየተለካ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱ በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ለ16ኛው ጊዜ ‹‹ወንድማማችነት ለሕብረብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የመገናኛ ብዙኃኑ የጋራ እሴቶች እኩልነትን፣ ማንነትንና አንድነትን በማጠናከር የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ትስስርን ከመጠበቅ አኳያ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ የዕለት ተዕለት እቅዳቸው አካል እንዲያደርጉና ሀገራዊ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ለፌዴራል መገናኛ ብዙሃንና ከኮሙዩኒኬሽን ቢሮዎች የተውጣጡ ሃላፈዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በቀረቡት የመወያያ ጽሑሮች ላይ የተለያዩ ሃሳብና አሰተያየቶች ተነሰተው ወይይት ተደርገውባቸዋል ፡፡