የገቢ ክፍፍል ቋሚ ኮሚቴ የገቢ ክፍፍል ቋሚ ኮሚቴ

የበጀት ድጎማና የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች አሉት፡ -

  1. በሕዝቦች እኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር እንዲሁም በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት እንዲመጣና አንድ ሀገራዊ ኢኮኖሚ ለመፍጠር የሚያስችል ዕቅድ ይነድፋል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  2. ድጎማና የጋራ ገቢዎች የሚከፋፈሉበትን ቀመር አስመልክቶ በጥናት ላይ የተመሠረተ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፤ ሲፀድቅም አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
  3. በሥራ ላይ ያለ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቀመር አፈፃፀምን እየገመገመ አስፈላጊ የማሻሻያ ሀሳቦችን ለምክር ቤት ያቀርባል፡፡
  4. የድጎማና የጋራ ገቢዎች የሚከፋፈሉበትን ቀመር ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ መረጃዎች በአግባቡ ተሰብስበው መቀመጣቸውን፣ መተንተናቸውን፣ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
  5. ተለይተው ያልተሰጡ የታክስና ግብር የመጣል ሥልጣኖችን አስመልክቶ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን መርምሮ ከሚመለከታቸው ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴዎች ጋር በመነጋገር በጥናት ላይ የተመሠረተ የውሳኔ ሀሳብ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ያቀርባል፡፡
  6. የድጎማ ቀመሩ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በማምጣት በኩል የተጫወተውን ሚና ለመገምገም የሚረዱ ጥናቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፡፡
  7. የገቢ ክፍፍል ወይም የድጎማ ቀመሩን አስመልክቶ አከራካሪ ነጥቦች ሲነሱ ወይም ቀመሩ እንዲሻሻል ጥያቄ ሲቀርብ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
  8. በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ስልጣንና ተግባራት በተጨማሪ ቋሚ ኮሚቴው

     ሀ. በተመሩለት ጉዳዮች ላይ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለም/ቤቱ የማቅረብ፣

     ለ. የተለያዩ አቤቱታዎች የማስተናገድ፣

     ሐ. በቀረቡለት ጉዳች ዙሪያ የሚመለከታቸውን አካላት የመጥራትና የማወያየት፣

     መ. የተለያዩ አውደ ጥናቶች እና ውይይት መድረኮችን ማዘጋጀትና የልምድ ልውውጥ የማድረግ እንዲሁም

     ሠ. ከምክር ቤቱና ከአፈጉባኤው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት የማከናወን አጠቃላይ ኃላፊነቶች ተሰጥተውታል፡፡

አሰተያየት እና ጥቆማ አሰተያየት እና ጥቆማ

Web Form with File Upload is temporarily unavailable.