የአፈ-ጉባኤመልዕክት የአፈ-ጉባኤመልዕክት

የአፈ-ጉባኤ መልዕክት

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፌዴራሉ መንግሥት አባል ክልሎች የሚገኙት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸው አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነው፡፡ ምክርቤቱ የሕገመንግሥት የበላይነት ሰፍኖ፣ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች በሁሉም መስክ እኩልነታቸውና የፈጣን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጦ፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሥር የሰደደ  አንድነት እና ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዳብሮ የማየት፣ ራዕይ ሰንቆና ሕገመንግሥቱን በመተርጎም፣ በመፈቃቀድ እና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሕዝቦች  አንድነት ሥር እንዲሰድ እና እንዲዳብር በማድረግ፣ በክልሎች መካከል ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ግንኙነቶችን በማዳበር፣ ፍትሀዊ እና ውጤታማ የድጎማ በጀት እና የጋራገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በማዘጋጀት እና በመወሰን፣ ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን በማጥናት እና በመለየት፣ እንዲሁም ዜጎች ሕገመንግሥቱን ጠንቅቀው አውቀው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት በቁርጠኝነት የመሥራት ተልዕኮ አንግቦ በሕገመንግሥቱ ተለይተው የተሰጡትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወጣትና ውጤታማ ለመሆን እየተጋ ይገኛል፡፡

የሕገመንግሥቱን የበላይነት ከማረጋገጥ አኳያ ሕገመንግሥቱን በመተርጎም፣ የሃብት ክፍፍሉ ፍትሓዊነት እንዲረጋገጥ የማከፋፈያ ቀመር ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍትሀዊ እና በሁሉም ተቀባይነት ያለው ቀመር ያዘጋጃል፡፡ ተደብቀው የነበሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በሕገመንግሥቱ እውቅና አግኝተው ማንነታቸው ተረጋግጧል፤ የቋንቋዎች ፤ የባህል እና የሀይማኖት እኩልነት በሀገሪቱ እንዲረጋገጥ ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እኩልነታቸውና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብሮላቸው ራስን በራስ ከማስተዳደርም በላይ በአገራዊ ጉዳዮች እኩል ተሳታፊ እና የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ብዝኃነትን በዴሞክራሲያዊ አግባብ በማስተናገድ በመቻቻል እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አገራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ምክር ቤቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ  አሰራሩን ከማሻሻል አኳያ ከአገራዊ እና አለማቀፋዊ ሁኔታዎች ለውጥ አንጻር ውስንነቶቹን እየፈተሸ ጠንካራ ተሞክሮዎችን በይበልጥ እያሸጋገረ እና የአገሮችን ስኬታማ ልምዶችን እየቀመረ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በተሸለ ሁኔታ በሚያረጋግጥ መልኩ ቀጣይ አሰራሮችን በአዲስ ለውጥ መንፈስ ለመሥራት በቁርጠኝነት ተዘጋጅቷል፡፡ ለተግባራዊነቱም ለምክር ቤቱ ድጋፍ የሚሰጠው ጽ/ቤቱን የእስካሁኖቹን መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የአሰራርና የአፈጻጸም ሁኔታዎችን በመፈተሸና በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡  ይሁን እንጂ ምክር ቤቱ  ይህንን ዓላማ በጽ/ቤቱ ውስን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ብቻውን ማሳካት ስለማይችል፤ የክልል መንግሥታት፣ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች፣ እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት የጎላ ተሳትፎ እንዳይለየው መልዕክቴን እስተላልፋለሁ፡፡

 

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ


Youtube Manager is temporarily unavailable.

የፌ/ም/ቤት ዩ-ቲዩብ ሥርጭት

የህገመንግስት ትርጉም የህገመንግስት ትርጉም

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ በካሄዳው 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን, 11/06/2020 Read More

ሚዲያ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓትና ሀገርን የማዳን ጥያቄ በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ውይይት ተካሄደ፤, 01/09/2021 Read More

ሕገመንግስቱ ለሴቶች ያጎናፀፋቸው የእኩልነት መብት, 23/01/2021 Read More

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሥልጣንና ተግባር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር እንደማይጣረስ ተገለፀ, 19/08/2020 Read More

ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም መሪ ሀሳብ ለሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ እየተሳተፉ ነው፡፡, 12/03/2020 Read More

ዴሞክራሲያዊ አንድነት ዴሞክራሲያዊ አንድነት

የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔሮችና ህዝቦ ቀን በዓል/ የህገ መንግስት ቀን/ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች, 08/11/2018 Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የክልልነት የህዝበ ውሳኔ ውጤትን መርምሮ አጸደቀ፤, 11/11/2021 Read More

የፌዴሬሽን ም/ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮረ አወደጥናት አካሄደ, 08/11/2018 Read More

የገቢ ክፍፍል የገቢ ክፍፍል

የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ዝግጅትን በተመለከተ የቀረበውን ዉሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ አጸደቀ።, 11/11/2021 Read More

አዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በአገራችን የፌዴራል ሥርዓታችን ጤናማና ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገለፀ ፤, 20/11/2020 Read More

የፌዴራል መሠረተልማት ክልላዊ ሥርጭት ፍትሐዊነትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ, 24/06/2020 Read More

አገራዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ሪፖርት ቀረበ, 11/06/2020 Read More

ሌሎች ሌሎች

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መስከረም 29 ይጀመራል, 08/11/2018 Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ንግግር, 15/11/2021 Read More

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሀገራቸውን ህልውና የማስጠበቅ ሀለፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ገለጹ።, 15/11/2021 Read More

ሁሉንም ዜጋ ያስደነገጠ ተግባር የተፈፀመበት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ታስቦ ዋለ።, 12/11/2021 Read More

በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፋ ተቋማዊ የአሰራር ሪፎርም የምክር ቤቱ ሕገመንግሥታዊ ተልዕኮውን ውጤታማ እንደሚያደርገው ተገለፀ ፤, 05/09/2021 Read More

የስብሰባ እቅዶች የስብሰባ እቅዶች

Pending Events Portlet is temporarily unavailable.