የዴሞክራሲያዊ አንድነት ቋሚ ኮሚቴ የዴሞክራሲያዊ አንድነት ቋሚ ኮሚቴ

  1. በሕዝቦች እኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተአንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር የሚያስችል አገራዊ አመለካከት እንዲፈጠር የሚያስችሉ ተግባራትን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡

  2. በክልሎቸ እንዲሁም በክልልና በፌደራል መንግስት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ የሚመሩለትን ጉዳዮች መርምሮ በሕ-ገመንግስቱና በሌሎች ሕጎች በተደነገገው መሰረት የውሳኔ ሀሳብ ለምክርቤቱ ያቀርባል፡፡

  3. ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሃብሔር ጉዳዮች በጥናት እንዲለዩ በማድረግ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

  4. የሕብረተሰቡን ንቃ-ሕገመንግስት ለማዳበር የሚያስችሉ ስልቶች እነዲቀየሱና የሕገ-መንግስት አስተምህሮ በተለያዩ ዙሪያዎች እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡

  5. ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣሉ ወይም ሊጥሉ የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በሚመለከታቸው አካላት ሊቀርብለት መርምሮ በጥናት ላይ በመመስረት የችግሮቹን መንስኤዎችና መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

  6. የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አከላለልን አስመልክቶ ለምክርቤቱ የሚያቀርበውን ረቂቅ መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

  7. ለተሰጠው ስልጣንና ተግባር አፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች የሚሰበስቡበትንና ጥናቶች የሚያካሂዱበትን ስልት እንዲቀየስ ያደርጋል፡፡ በስራላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

  8. በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

አሰተያየት እና ጥቆማ አሰተያየት እና ጥቆማ

እባክዎ አሰተያየት እና ጥቆማዎትን በዚህ ቅጽ ይላኩልን. ከአንድ በላይ አባሪ ካሎት ወደ አንድ ቀይረው (ዚፕ አድርገው) ይላኩ፡፡

This field is mandatory.
This field is mandatory.
Text to Identify Refresh CAPTCHA Refresh CAPTCHA