ሥለ ቋሚ ኮሚቴዎች ሥለ ቋሚ ኮሚቴዎች

  1. ም/ቤቱ የሚከተሉት ቋሚ ኮሚቴዎች ይኖሩታል፡-

       ሀ. የህገመንግስትና የክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ

       ለ. የድጐማ በጀትና የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ

  1. ቋሚ ኮሚቴዎች ተጠሪዎታቸው ለም/ቤቱ ነው፡፡
  2. እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢን ከም/ቤቱ በአፈጉባኤው አቅራቢነት የፌዴሬሽን ም/ቤት በአባላቱ መካከል የሚመርጣቸዉ 15 አባላት ይኖሩታል፡፡ አባላቱ ከመካከላቸው አንድ ጸሐፊ ይመርጣሉ፡፡
  3. አንድ የም/ቤት አባል በአንድ ጊዜ ከአንድ ቋሚ ኮሚቴ በላይ አባል ሆኖ ሊሠራ አይችልም፡፡
  4. የቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች ተጠሪነታቸዉ ለኮሚቴው እና ለአፈ ጉባኤው ይሆናል፡፡
  5. የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚከተሉትን አጠቃላይ ስልጣንና ተግባር አሏቸው፡፡

       ሀ. በተመሩላቸው ጉዳዮች ላይ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለም/ቤቱ ማቅረብ፣

       ለ. የተለያዩ አቤቱታዎች ማስተናገድ፣

      ሐ. በቀረቡላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚመለከታቸውን አካላት የመጥራትና የማወያያት፡፡

      መ. የተለያዩ አውደ ጥናቶችን እና የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ፡፡

      ሠ. ከምክር ቤቱና ከአፈ ጉባኤው የሚሰጧቸውን ሌሎች የግባራት ማከናወን፡፡