4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 04/2012 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓቢሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ የጋራ ስብሰባ 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተራዘመው የህዝብና ቤት ቆጠራ አሁንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለህዝብ ጤናና ደህንነት ሲባል ለሶስተኛ ማራዘም ማስፈለጉን ተገልጿል።የምክር ቤቶቹ አባላት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቆጠራው እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በ5 ተቃውሞ፣ በ13 ድምጸ ታዕቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል::