15ኛውየኢትዮጵያብሔሮች፣ብሔረሰቦችናሕዝቦችቀን በዓልበብዝኃነትናበእኩልነትየተመሰረተአገራዊአንድነትንለማጠናከር በሚያስችልመልኩእንደሚከበርተገለፀ

የ15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴና የአስተናጋጁ ድሬደዋ አስተዳደር ኮሚቴ በጋራ እቅድ ዙሪያ ተገናኝተ ውውይይት አድርገዋል፡፡ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ ዕለቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት የፀደቀበት ህዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ሆኖ በየዓመቱ በድምቀት እንዲከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዚያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም መወሰኑን አውስተው በዓሉ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ፣ ባህለዊ እሴቶቻቸውን እንዲያስተዋወቁ፣ ማህበራዊ ግንኙነታቸው እንዲጠናከር ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ልማታዊ መነቃቃትንና ተነሳሽነትን እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡ 
በተጨማሪም በዓሉ በሕገ መንግስቱና ሕገመንግስታዊ ሥርዓት ዙሪያ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም አስገንዝበዋል፡፡ 
በዓሉ ለ14 ተከታታይ ዓመታት የተከበረ ቢሆንም በተለይም አገራዊ አንድነትንና በሕገመንግስቱ ላይ አገራዊ መግባባትን ከመፍጠር እና በዓሉን በአለም አቀፍ ደረጃ ከማስተዋወቅ አኳያ ውስንነቶች እንደ ነበሩበት አልሸሸጉም፡፡ 15ኛው በዓል ከዚህ ቀደም የታዩትን ውስንነቶች በማረም ጠንካራጐኖችን በማጐልበት በተለይም አገራዊ አንድነትን፣ የርስ በርስ ግንኙነትንና፣ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ሊያስቀጥል በሚችል መልኩ በብሔርና በኢትዮጵያዊ ማንነቶች መካከል ሚዛን ለመጠበቅ እና አገራዊ ሪፎርሙ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶበት እንዲከበር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ 
“በዓሉበዋናነት የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች የመጀመሪያ የአገራችን ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር የሚረዱና የሚያጠናክሩ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በሕገመንግስቱና በፌዴራል ስርዓቱ ላይ አሰተምህሮት እና ስርጻት ስራዎች ላይ በመስራት በአገር አቀፍ ደረጃ በሕገ መንግስቱ ላይ ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚረዱ ለማክበርነው“ ሰሉ አፈ ጉባዔው ተናግረዋል፡፡ 
በድሬደዋአስተዳደርአስተናጋጅነትየሚከበረው 15ኛው በዓል የትውልድ አሻራ የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት በስኬት በተጠናቀቀበት እና የሲዳማ ክልል 10ኛ የፌዴሬሽኑ አባል ክልል ሆኖ በፀደቀበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ ልዩ እንሚሆንና ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡በማከልም ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ከመከላከል አንጻርም አፅዕኖት የተሰጠ ሲሆን ወጪ ቆጣቢ እንዲሆንም አቶ አደም ፋራህ አሳስበዋል፡፡ 
የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ በበኩላቸው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችእና ሕዝቦች ቀን በዓል የተለያዩ ባህልና ወግ ያላቸውን ህዝቦች በአንድ ቦታ አሰባስቦ የሚያገናኝ የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ገፅታና የብዝኃነት ፀጋ ጐልቶ የሚገለፅበት መድረክ በመሆኑ አንድነታችንን በማጠናከር ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የምናደርግበት ትልቅ ትርጉም ያለው በዓል በመሆኑ በትኩረታና ኮቪድ 19 ከመከላከል ረገድ በጥንቃቄ ይከበራል ብለዋል፡፡ 
በውይይት መድረኩ የአዲስአበባእና የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤዎችን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች አፈጉባኤዎች የተሳተፉበት ሲሆን በመጨረሻም የደሬደዋ አስተዳደር የልማት ስራዎች ጉብኝትና የአረንጔዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት በማከናወን ተጠናቅቋል፡፡ 
                                                         ሰኞ ነሐሴ 4/ 2012 ዓ.ም