የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህገ-መንግስት እና የፌዴራሊዝም አስትምህሮ ማዕከል የማቋቋሚያ አዋጅን ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት5 2011(ኤፍ..) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህገ-መንግስት እና የፌዴራሊዝም አስትምህሮ ማዕከል የማቋቋሚያ አዋጅን አፀደቀ።

የህዝብ ተወካች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የህገ መንግስት እና የፌዴራሊዝም አስትምህሮ ማዕከል ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቷል።

ረቂቅ አዋጁን በህግና ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፎዚያ አሚን ለምክር ቤቱ አቅርቧል።

የማዕከሉ መቋቋም የህገ-መንግስትና የፌዴራሊዝም ፅንስ ሀሳቦችን በማስረፅ በህገ መንግስታዊ መርሆችን በመከተል መብቱን የሚያስከብርና የሚጠይቅ ማህበረሰብ ለመፍጠርር የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም የፌደራሊዝም ስርዓትን ለማስፈን፣ ዲሞክራሲያዊ አሰራርን ለማጠናከርና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በውይይት ለመፍታት ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ማዕከሉ መልካም የሆኑ ሀገራዊ እሴቶችን በማጎልበት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ነው የተባለው።

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላም የፌዴራሊዝም አስትምህሮ ማዕከል የማቋቋሚያ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

ምንጭ፤ ፋና ብሮድካስትንግ