ኢትዮጵያናራሺያ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጻ፡፡

ኢትዮጵያናራሺያ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጻ፡፡
ኢትዮጵያናራሺያ ረዥም ዘመናት ያስቆጠረውን  የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጻ፡፡ይህን የገለጹት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክርቤትአፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ አደምፋራህ በኢትዮጵያ የራሺያ አምባሳደር የሆኑትን  ክቡር ኤቭጌልፕሪኮንን በቢሮችው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅትነው፡፡ አፈጉባዔው ከራሺያ አቻቸው ከክብርት ማትቪየንኮ የተላከላቸውን የእንኳን ደስ አለዎት መልክት ከአምባሳደሩ እጀ አመስግነው ተቀብለዋል፡፡
በቆይታቸውም ሁለቱ ምሀገሮች ከ1897 ዓም ጀምሮ ጠንካራ እና ረጀም ዘመናትን የዘለቀ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስር እና ግንኙነት እንደነበራቸው በማወሳት ራሺያ ለኢትዮጵያ ላደረገቸው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እና ትብብር ክቡር አፌጉባዔው አመሰግነዋል፡፡
የራሺያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት በይጠልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የትብብር እና የመግባብያ ሰነድ ያዘጋጅች መሆኑን የጠቀሱት ክቡር አምባሳደርሩ በሰነዱ ዙርያ በኪጋሊ በሚካሄደው በአለም አቀፉ የፖርላማዎች/IPU/ ህብረት ስብሰባ ላይ ተገነኝተው እንደሚወያዩበት እና ቀጥሎም በራሺያ ሞስኮ እንደሚፈራረሙ ተናግናዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እነዳለ የተከበሩ አፈጉባዔ የፌዴሬሽን  ምክርቤት በአሰራር ሪፎርም ሄደት ላይ እንዳለ ገልጻው ይህንኑ ለማጠናከር የአቅምግንባታ ፤የልምድል ውውጥና ድጋፉ እንደሚያስፈልግ የተናገሩ ሲሆን ከዚህ አኳያ ከተለያዩ የስራሃላፊዎች ጋር የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም እንደሚመቻች አምባሳደሩ ተናግረዋል፤በጋራ ለመስራትም ያላቸውን ፍላጎት አሳይቷል፡፡
በተያያዘ ዜና ሚሰተር ኪሊም ካውንሲል ኦፍ ራሺያ ፌዴሬሽን የገዠው ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሲሆኑ በቅርቡ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኘ ጠቅሰው በለሎች የትብብር ማዕቅፎች፤በቋሚ ኮሚቴዎች አሰራር፤ በመንግስታ ችግኑኘት እና በገቢ ክፍፍል ቀመር ዙሪያ የአቅም ግንባታና የልምድ ልውውጥ እንደሚያዳርጉ ገልጻዋል፡፡
                             ሐምሌ 09/2012 ዓ.ም
                              አዲስ አበባ