ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም መሪ ሀሳብ ለሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ እየተሳተፉ ነው፡፡

ለመድረኩ ተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር አፌ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ እብራሂም እንዳሉት ሕገ-መንግሥቱና የፌዴራል ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያስገኘላቸው ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎቹና ትሩፋቶች በርካታ ሲሆኑ በተለይም ለፆታ እኩልነት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የሴቶች እኩልነት ህገመንግስታዊ ዋስትና ኣግኝቶ ከማጀት ወጥተው በየደረጃው ያለውን የውሳኔ ሰጭነቱ ጀምሮ በኢኮኖሚና በማህበራዊም ተሳታፊነታቸውና ተጠቃሚነታቸው እውን ለማድረግ ባደረጉት ጥረት በርካታ ጠቀሜታ ተጎናፅፈዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ወጣቶች የአገር ተረካቢዎች እንደመሆናቸው መጠን በግብረገብ ተኮትኩተው ማደግ፣ በምርምርና በፈጠራ መስኮች ወጣት ምሁራንን ማፍራት እንዳለብን አንዱ የፖሊሲያችን አቅጣጫ ኣድርገን ሰፊ ስራ በመስራት በወጣቶች ላይም ሁለገብ ለውጥ ለማምጣት ተጥረዋል፡፡ ምንም እንኳ ለወጣቶች በቂ የሥራ ዕድል ከመፍጠርና ከማመቻቸት ረዥም ርቀት ባንጓዝም የወጣቶችን የትምህርት ዕድልና ልማት ከማስፋት አኳያ በአገራችን በሁሉም ክልሎች የትምህርት ተደራሽነቱንና ፍትሐዊነቱን ከማረጋገጥ ሕገመንግሥቱ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ስሉ ገልፀዋል፡፡