የፌዴሬሽን ም/ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮረ አወደጥናት አካሄደ

ግጭቶች ከመከሰታችው በፊት አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የግጭት ካርታ ጥንቅር እየተዘጋጀ መሆኑን  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት አሰታወቀ ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት  ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮረ አወደጥናት በጌዲዮ ዞን በዲላ ከተማ አካሄዷል።

በአገራችን ውስጥ የማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ ስርዓት ከማንነታችው ጋር የተዋሃደ የባህል ባለቤቶች ልዩ መገለጫ እስከ መሆን የደረሰ የግጭት አፈታት ሀገር በቀል ዕውቀት በጊዜ ሂደት ጎልብቶ በትውልዶች ቅብብሎሽ ዘመን ተሻጋሪ ላይ ደረሷል። አሁን ወጣቱ ትውልድ እነዚህ ባህላዊ እሴቶችን አውቆ እንዲተገብሯቸው ከማድረግ አንጻር ብዙ ሊሰሩ እንደምገባ መሆኑ የአወደጥናቱ ተሳታፉዎች እንዲ ሲሉ ገልጻዋል ‘‘ከአባቶታችን የወረስን ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት አሁን ያለው ወጣቱ ትውልድ አያወቅም፤የሚናሳወቃቸው ግን እኛው ነን ከአባቶች እንደወረሰነው አሁን ያለው ትውልድ አሁንም በሽንጎ ስርዓታችን ማስተማር ይገባናል’’ በማለት ተናግዋል ።

በአወደ ጥናቱ  በጉጂ ኦሮሞ እና ጌዲዮ ህዝቦች መካከል ባለ ባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ያተኮረ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀረቦው ወይይት ተደርጎባቸው  ተሳታፊዎች ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች መካከል አንዱ ‘‘ጎንደሮ’’ የሚባል የግጭት አፈታት ዘመናዊ የግጭት አፈታት ስርዓት ጋር ጎን ለጎን በመጠቀም መንግስት ጋር አብሮ የሚያሰራ ሁነታ መፈጠር አለበት ሲሉ አሰተያየት ሰጠዋል። የጥናታዊ ጹሑፍ አቅራብው አቶ ጸጋዬ ታደሰ የጥናታቸው አጠቃላይ ምልከታ መነሻ በማድረግ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓት እውቀቶችን ተቀብሎ በማሰቀጠል ረገድ እጥረቶች እንዳሉ በመግለጽ አሁን በአገራችን ትናንሽ ምክናቶችን የግጭት መነሻ እየሆኑ መሆኑን እንዲ ሲሉ ይናገራሉ በተለይም በወጣቱ አከባቢ ላይ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓት እውቀቶችን ሽግግር ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት አባቶችም ዕውቀቶችን ከማሽጋገር አኳያ ችግሮች እንዳሉ በጥናቱ ታይቷል።

በማህበረሰብ ውስጥ ያሉት እምቅ ዕውቀቶች በጥናትና ምርምር በማሳደግ ከዘመኑ ከሕግ ስርዓቶች ጎን ለጎን በአማራጭነት በመተግበር በሚፈለገው ሠላም ዙሪያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትኩረት አደረጎ ሊሰሩ እንደሚገቡ የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ ወ/ሮ መህቡባ አደም እንድህ ሲሉ ገልጻል ‘‘እንድ ዓይነት ግጭት መፍቻ ዜደዎች በአግባቡ በመጠቀም ያሉብንን ችግሮች በመፍታት ትልቅ ሚና አለው በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶች በመጠቀም ጥናትና ምርምር ማድረግ አለባቸው’’ ሲሉ ገልጻዋል።

በአወደ ጥናቱ ላይ የተገኙት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት የዲሞክራሲ አንድነት፣የሕገ መንግስት አስተምህሮና የሠላም ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ክብርት ወ/ሪት ፍሬወይኒ ገብረእግዚአብሔር  ምክር ቤቱ ግጭቶችን ከመከሰታችው በፊት አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የግጭት አፍታት ጥንክር ካርታ ዝግጅት መጀመሩን ገልጾዋል።በተላያዩ ምክንያቶች ወቅታዊ ሁነታዎች አሁን ያሉት ግጭቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁኔታዎቹ ስለተቀየሩ ግጭቶችን ለመከላከል የሚያስችሉት Strategy ስርዓት ለመዘርጋት በእንቅስቃሰ ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልዋጾል። በአውደ ጥናቱ ላይ አባ ገዳዎች ፣የሃይማኖት አባቶች ፤ ሙሁራን እና ጥሪ የተደረጋላቸው እንግዶች ተሳትፋዋል።

ጥቅምት 2/2011 ዓ.ም, ዲላ