የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች አባላትና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አረጋገጡ፤

ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓ/ም "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ቃል የ2 ደቂቃ ፕሮግራም እንዲኖር በኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የተደረገውን ጥሪ በመቀበል የሁለቱ ም/ቤቶች አባላትና ሰራተኞች አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
በም/ቤቱ ቅጥር ግቢ ከጠዋቱ 5:30 ላይ በነበረው ስነ-ስርዓት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ እንዲሁም የሁለቱም ም/ቤቶች አባላትና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፤ ሁሉም በያሉበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ለአንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ እያጨበጨቡ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና አጋርነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ህግን ለማስከበር ተሰማርቶ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ ላለው ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ክብር በመስጠት እንዲሁም፤ በህዝብና መንግስት የተጣለባቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ሀይል ክህደት የተሰዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ተዘክረዋል፡፡
ህዳር/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ