የህገመንግስት ትርጉም የህገመንግስት ትርጉም

ሚዲያ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓትና ሀገርን የማዳን ጥያቄ በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ውይይት ተካሄደ፤, 01/09/2021 Read More

ሕገመንግስቱ ለሴቶች ያጎናፀፋቸው የእኩልነት መብት, 23/01/2021 Read More

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሥልጣንና ተግባር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር እንደማይጣረስ ተገለፀ, 19/08/2020 Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ በካሄዳው 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን, 11/06/2020 Read More

ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም መሪ ሀሳብ ለሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ እየተሳተፉ ነው፡፡, 12/03/2020 Read More

ዴሞክራሲያዊ አንድነት ዴሞክራሲያዊ አንድነት

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የክልልነት የህዝበ ውሳኔ ውጤትን መርምሮ አጸደቀ፤, 11/11/2021 Read More

የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔሮችና ህዝቦ ቀን በዓል/ የህገ መንግስት ቀን/ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች, 08/11/2018 Read More

የፌዴሬሽን ም/ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮረ አወደጥናት አካሄደ, 08/11/2018 Read More

የገቢ ክፍፍል የገቢ ክፍፍል

የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ዝግጅትን በተመለከተ የቀረበውን ዉሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ አጸደቀ።, 11/11/2021 Read More

አዲሱ የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በአገራችን የፌዴራል ሥርዓታችን ጤናማና ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገለፀ ፤, 20/11/2020 Read More

የፌዴራል መሠረተልማት ክልላዊ ሥርጭት ፍትሐዊነትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ, 24/06/2020 Read More

አገራዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ሪፖርት ቀረበ, 11/06/2020 Read More

ሌሎች ሌሎች

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እስተፌን ሁርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል ረዥም ጊዜ የቆየ የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የፓርላሜታዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በቀጣይም ከጀርመን መንግስትና ሕዝብ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንድቀጥል የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ እያደረገ ያለውን ድጋፉና ትብብር በማድነቅ አፈ ጉባዔው አመሰግነዋል፡፡
ጀርመንና ኢትዮጵያ ከ1905 እአአ ጅምሮ ይፋዊ የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት የጀመሩና ጀርመን በተለያዩ መርሃ ግብሮች የኢትዮጵያ የልማት አጋር በመሆን ቀጥላለች፡፡ ሁለቱም አገራት የሚከተሉት የፌዴራል ስርዓት ባለ ሁለት ምክር ቤቶች በመሆኑ ከጀርመን መንግስት ጋር የፌዴራል ስርዓት እንዲጎለብት በጋራ ለመሰራት የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ክብር አቶ አደም ፋራህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔው ገልጸዋል፡፡
ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የምጣኔ ሀብት እና ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላትና በተለይም የሁለቱ አገራት የንግድ ትስስር በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመጥቀስ የጀርመን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ስለዚህ ይህንኑ አጠናክሮ የሚቀጥሉ መሆኑን አምባሳደር እስተፌን ሁር ገልጸዋል ።
አምባሳደር እስተፌን ሁር የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሪፎርሞች እጅግ የሚበረታታ መሆኑን አድንቀው ለስኬታማነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጀርመን መንግስት የልማት ድጋፍና ትብብር እንደማይለየው አስረድቷዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያና በጀርመን መንግስታት መካከል የቆየ ታሪካዊ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደ በላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አምባሳደር እስተፌን ሁር ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በውይይታቸው የጀርመን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት /IGAD/ ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማትና ዕድገት እንዲኖረው በትብብር ለመስራት በመምከር ስምምነት ላይ ደርሷዋል፡፡
ጥር/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ