የአፈ-ጉባኤመልዕክት
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፌዴራሉ መንግሥት አባል ክልሎች የሚገኙት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸው አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነው፡፡ ምክርቤቱ የሕገመንግሥት የበላይነት ሰፍኖ፣ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች በሁሉም መስክ እኩልነታቸውና የፈጣን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጦ፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሥር የሰደደ አንድነት እና ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዳብሮ የማየት፣ ራዕይ ሰንቆና... Read More
የህገመንግስት ትርጉም
የገቢ ክፍፍል
ሌሎች
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እስተፌን ሁርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል ረዥም ጊዜ የቆየ የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የፓርላሜታዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በቀጣይም ከጀርመን መንግስትና ሕዝብ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንድቀጥል የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ እያደረገ ያለውን ድጋፉና ትብብር በማድነቅ አፈ ጉባዔው አመሰግነዋል፡፡
ጀርመንና ኢትዮጵያ ከ1905 እአአ ጅምሮ ይፋዊ የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት የጀመሩና ጀርመን በተለያዩ መርሃ ግብሮች የኢትዮጵያ የልማት አጋር በመሆን ቀጥላለች፡፡ ሁለቱም አገራት የሚከተሉት የፌዴራል ስርዓት ባለ ሁለት ምክር ቤቶች በመሆኑ ከጀርመን መንግስት ጋር የፌዴራል ስርዓት እንዲጎለብት በጋራ ለመሰራት የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ክብር አቶ አደም ፋራህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔው ገልጸዋል፡፡
ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የምጣኔ ሀብት እና ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላትና በተለይም የሁለቱ አገራት የንግድ ትስስር በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመጥቀስ የጀርመን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ስለዚህ ይህንኑ አጠናክሮ የሚቀጥሉ መሆኑን አምባሳደር እስተፌን ሁር ገልጸዋል ።
አምባሳደር እስተፌን ሁር የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሪፎርሞች እጅግ የሚበረታታ መሆኑን አድንቀው ለስኬታማነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጀርመን መንግስት የልማት ድጋፍና ትብብር እንደማይለየው አስረድቷዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያና በጀርመን መንግስታት መካከል የቆየ ታሪካዊ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደ በላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አምባሳደር እስተፌን ሁር ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በውይይታቸው የጀርመን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት /IGAD/ ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማትና ዕድገት እንዲኖረው በትብብር ለመስራት በመምከር ስምምነት ላይ ደርሷዋል፡፡
ጥር/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ